ማስታወቂያ
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት የፕሬዚዳንት፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት እና የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዚዳንትነት ክፍት የአመራርነት ሥራ መደቦች ላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መመደብ መሾም/መሰየም፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተቀመጠውን ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ እና ከስር የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በዌብሳይትና፣ በማህበራዊ ሚዲያ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የስራ ቀናት በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 116 ወይም በአዲስ አበባ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ
ሀ. ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመጣ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ ኖሮት የረዳት ፕሮፌሰርነት ወይም በህኪምና ሙያ ስፔሻሊቲና በዚህ ደረጃ አቻ የሆነ የአከደሚክ ማዕረግና ከዚያ በላይ ያለው መሆን ይኖርበታል፣
- ሁለተኛ ዲግሪ ኖሯቸው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሚመጡ ሴት እጩ ተወዳዳሪዎች የአካዳሚክ ማዕረግ ሳይጠበቅባቸው ለፕሬዝዳንትነት ክፍት የአመራርነት መደብ ሊወዳደሩ ይችላሉ ፣
- በፕሬዝዳንትነት 2 ዓመት ወይም በምክትል ፕሬዝዳንትነት 3 ዓመት ወይም በኮሌጅ ዲንነት 3 ዓመት ያገለገለ/ች መሆን ይኖርበታል፣
- ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ወይም ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚመጣ ተወዳዳሪ በአመራርነት የስራ መደብ በሰራበት መስሪያ ቤት የመራው የሰራተኞች ብዛት፣ ያመነጨውና ያስተዳደረው የበጀት መጠን ከተቋሙ ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል፣
- ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚመጡ እጩ ተወዳዳሪዎች የሚጠበቀው ዝቅተኛ የስራ ልምድ በበላይ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፣ በከፍተኛ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፣ በዋና እና በምክትል ዋና ዳይሬክቴሪነት ወይም በዋና ስራ አስፈፃሚነት እና ከዚህ ጋር አቻ በሆኑ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ቢያንስ 8 ዓመት አገልግሎት የሰጠ/ች መሆን ይኖርበታል፡፡
- ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች፣
- ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ የሚያስፈጽም ስትራቴጂክ እቅድ በማስተማሪያ ቋንቋ አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል፣
- በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለተከታታይ ሁለት ተርም ያገለገሉ በፕሬዝዳንትነት አመራርነት ስራ መደብ ላይ መወዳደር ይችላሉ፣
- በአንድ ተቋም ዉስጥ በፕሬዝዳንትነት ወይም በምክትል ፕሬዝዳንትነት በመስራት ላይ ያለ አመራር በራሱ ተቋም በበሚወጡ ተመሳሳይ የዉድድር መደቦች ላይ ለመወዳደር አይችልም፡፡ ሆኖም በሌላ ተቋማት በሚወጡ ክፍት የአመራር መደቦች ማስታወቂያ ላይ መወዳር ይችላል፤
- ከዚህ በፊት በመንግስት ዩኒቨርሲቲ በፕሬዝዳንትነት ለተከታታይ ሁለት ተርም ያላገለገለ/ች፣
- ለወጣው ክፍት የአመራር ስራ መደብ የጡረታ ጊዜው ሳይደርስ ሙሉ ስድስት ዓመት ማገልገል የሚችል መሆን አለበት/ባት፣
ለ. ለአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንትነት እና ለምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደር
- ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመጣ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የሶስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) የትምህርት ዝግጅት ያለዉ እና የረዳት ፕሮፌሰርነት ወይም ከዚያ በላይ የአካዳሚክ ማዕረግ ያለው መሆን ይኖርበታል፣
- ሶስተኛ ዲግሪ ኖሯቸው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሚመጡ ሴት እጩ ተወዳዳሪዎች የአካዳሚክ ማዕረግ ሳይጠበቅባቸው ለፕሬዝዳንትነት ክፍት የአመራርነት መደብ ሊወዳደሩ ይችላሉ፣
- በም/ፕሬዝዳንትነት 2 ዓመት ወይም በኮሌጅ ዲንነት/ በአከደሚክ ዘርፍ በዳይሬክተርነት 3 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/ች መሆን ይኖርበታል፣
- ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ወይም ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚመጣ ተወዳዳሪ በአመራርነት የስራ መደብ በሰራበት መስሪያ ቤት የመራው የሰራተኞች ብዛት፣ ያመነጨውና ያስተዳደረው የበጀት መጠን ከተቋሙ ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል፣
- ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚመጡ እጩ ተወዳዳሪዎች የሚጠበቀው ዝቅተኛ የስራ ልምድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ ለ10 ዓመት የማስተማርና ምርምር ልምድ ያለዉ/ት፣
- ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚመጡ እጩ ተወዳዳሪዎች የሚጠበቀው ዝቅተኛ የስራ ልምድ በበላይ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፣ በከፍተኛ አመራርነት ቢያንስ 5 ዓመት፣ በዋና እና በምክትል ዋና ዳይሬክቴሪነት ወይም በዋና ስራ አስፈፃሚነት እና ከዚህ ጋር አቻ በሆኑ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ቢያንስ 8 ዓመት አገልግሎት የሰጠ/ች መሆን ይኖርበታል፡፡
- ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች፣
- ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ የሚያስፈጽም ስትራቴጂክ እቅድ በማስተማሪያ ቋንቋ አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል፣
- በአንድ ተቋም ዉስጥ በፕሬዝዳንትነት ወይም በምክትል ፕሬዝዳንትነት በመስራት ላይ ያለ አመራር በራሱ ተቋም በበሚወጡ ተመሳሳይ የዉድድር መደቦች ላይ ለመወዳደር አይችልም፡፡ ሆኖም በሌላ ተቋማት በሚወጡ ክፍት የአመራር መደቦች ማስታወቂያ ላይ መወዳር ይችላል፤
- ለወጣው ክፍት የአመራር ስራ መደብ የጡረታ ጊዜው ሳይደርስ ሙሉ አራት ዓመት ማገልገል የሚችል መሆን አለበት/ባት፣
- እጩ ተወዳዳሪው በከባድ ወንጀሎች እና ከባድ የዲስፕሊን ጉድለት ክስ ወይም ጥፋት የሌለበት መሆን አለበት/ባት፣
- የምልመላ ውጤት፣ የቃል ፈተና ጊዜ እና ቦታ በተመዘገቡበት የምዘገባ ማዕከል በማስታወቂያ ሰሌዳ ይገለፃል፣
የማመልከቻ አቀራረብና የሚያስፈልጉ ሰነዶች
ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ሰነዶች አያይዘው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ/ በዌየብ ሳይት/በማህበራዊ ሚዲያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡-
- የሕይወት ታሪክ (CV) እና የትምህርት ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ (1)
- የሥራ ልምድ እና የአመራርነት አገልግሎት ማረጋገጫ ሰነድ፣
- የዩኒቨርሲቲ መምህር ከሆኑ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ ያሳተሟቸው የምርምር ስራዎች አርትኦት የተደረጉ አርትክሎች፤
የምዝገባ ጊዜ
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ/በዩኒቨርሲቲዉ ወብ ሳይት/ በማህበራዊ ሚዲያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል፣
የምዘገባ ቦታ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 116
- አዲስ አበባ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
- ለበለጠ መረጃ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሚመዘገቡ በስልክ ቁጥር 0917854875 እንዲሁም በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚመዘገቡ በስልክ ቁጥር 0911083067 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የኢሜይል አድራሻ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. - ወብሳይት https:// wollegauniversity.education.et ስካን የተደረገ ፒዲኤፍ ሰነድ መላክ ይኖርበታል፡፡
- የተቋሙ ፖ.ሣ.ቁ 395